በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ፣ ትላንት ንጋት ላይ አምስት ሰዎች በታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡
የትላንቱ ግድያ የተፈጸመው፣ በወረዳው 36 ሰላማዊ ሰዎች ከተገደሉ ከቀናት በኋላ ነው፡፡ ግድያው መቀጠሉን ተከትሎ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እንደጨመረ፣ አስተያየት ሰጪው ገልጸዋል፡፡
ዐዲስ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ፣ ከክልሉ መንግሥት መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡
በተያያዘ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ፣ ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ በምሥራቅ አርሲ “በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመ” ያለውን ጥቃት እና ግድያ አውግዟል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።