የኒዤር ሁንታ ባዙምን እንዲለቅ ናይጄሪያ ጠየቀች

ፕሬዝደንት ሞሃመድ ባዙም (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)

የኒዤር ወታደራዊ ሁንታ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ፕሬዝደንት ሞሃመድ ባዙምን እንድሊቅ እና ወደ ሶሶተኛ አገር እንዲሄዱ እንዲፈቅድ ናይጄሪያ ጥያቄ አቅርባለች፡፡

ናይጄሪይ የወቅቱ የየቀጠናው የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኤኮዋስ) ሊቀ መንበር ነች፡፡ የሐምሌውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ፣ ኤኮዋስ በኒዤር ላይ ማዕቀብ ጥሏል።

ኤኮዋስ ባዙም ወደ ስልጣናቸው እንዲመለሱ ጥሪ ቢያቀርብም፣ ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመመለስ እስከ ሶስት ዓመት ያስፈልገኛል በሚል ወታደራዊ ሁንታው ባዙምን አግቶ ቆይቷል።

“ፕሬዝደንት ባዙም ኒዤርን ለቀው መውጣት እንዲችሉ ጥያቂያችንን አቅርበናል” ሲሉ የናይጄሪያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሱፍ ቱጋር ለአገር ውስጥ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተናግረዋል።

“ወደ ሶሶተኛ አገር እንዲሄዱ ከተደረገ በኋላ፣ ማዕቀቡን ስለማንሳት እንነጋገራለን” ብለዋል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

የኤኮዋስ መሪዎች የዛሬ ሳምንት እሁድ በናይጄሪያ ጉባኤ እንደሚቀመጡ ተነግሯል። ባለፉት ሶስት ዓመታት በማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ እና ኔዢር መፈንቅለ መንግስት ስላስተናገደው ቀጠና ይወያያሉ ተብሏል።