በማዳበርያ እጥረት እና በዝናም መብዛት ምርታቸው እንዳሽቆለቆለ አርሶ አደሮች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፈው የመኸር ምርት ዘመን፣ የአፈር ማዳበርያ በወቅቱ እና በበቂ መጠን ባለመቅረቡ፣ በምርታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን አርሶ አደሮች ገልጸዋል።

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ለተገኘው የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ፣ አርሶ አደሮቹ እንደተናገሩት፣ በግብአት እጥረቱ የተነሣ የዘንድሮው ምርት ቢያንስ በግማሽ አሽቆለቁሏል፤ ከዚያም በኋላ ያለወቅቱ የጣለው ዝናብም፣ የምርት አሰባሰቡን አስተጓጎሎባቸዋል።

የማዳበሪያ እጥረቱን ለማካካስ፣ አርሶ አደሩ፣ ባህላዊ ማዳበሪያንና የተለያዩ ዘዱዎችን እንዲጠቀም መደረጉን የወረዳው አስተዳደር ሲገልጽ፤ የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ በበኩሉ፣ የግብአት እጥረቱ በክልል ደረጃ በዘንድሮው ምርት ላይ ያደረሰው ተጽእኖ የለም፤ በስፋት ለማምረት ዕቅድ የተያዘባቸውና የደረሱ ሰብሎችንም ለመሰብሰብ ርብርብ እየተደረገ ነው፤ ብሏል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።