ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ሱዳናውያን ሴቶች፣ ላለፉት ሰባት ወራት በሀገራቸው ላይ እየተካሄደ ስላለው አስከፊ ጦርነት ለመነጋገር ናይሮቢ ላይ ተሰባስበው ነበር። ማቆሚያ ያለው በማይመስለው ጦርነት ድምፃቸው መታፈኑን ያመለከቱት እነዚህ ሴቶች፣ ከሚያዚያ ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለውን እና በሚሊየን የሚቆጠሩትን ያፈናቀለውን ግጭት ለመፍታት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።
የአሜሪካ ድምፅ የናይሮቢ ቢሮ ኃላፊ ማሪያማ ዲያሎ ያደረሰችንን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች።