በዐዲስ አበባ፣ ከሳምንት በፊት በተካሔደው 23ኛው ዙር “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” ላይ ከተሰሙ የተቃውሞ ድምፆች ጋራ በተያያዘ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደኾነ፣ ጠበቃቸው ገለጹ፡፡
በአንድ ቦታ የሚገኙት የታሳሪዎች ቁጥር 19 መድረሱን የገለጹት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ፣ እስከ አሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡም ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ ለፍርድ ሳያቀርባቸው የቆየው፣ ጉዳዩን ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋራ አገናኝቶት ሊኾን እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡
የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው አመልክተዋል፡፡ ታሳሪ ወንድማቸው የፖለቲካ ተሳትፎ እንደሌለው የገለጹ አስተያየት ሰጪ፣ እስከ አሁን ለፍርድ ሳይቀርብ በእስር ላይ እንደሚገኝና ቤተሰቡም እንደተጨነቀ ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከፖሊስ አስተያየት ለማግኘት ዛሬም ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።