ፓስፖርት የሚጠባበቁ አመልካቾች በሙሉ ፈጥነው ይስተናገዳሉ ሲል ተቋሙ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ጠይቀው እየተጠባበቁ ያሉ አመልካቾችን፣ እስከ ታኅሣሥ ወር ድረስ ሙሉ በሙሉ እንደሚያስተናግድ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ፣ የፓስፖርት አገልግሎት ማግኘት እጅግ ከባድ እንደኾነ፣ የሰነዱ ፈላጊዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ፣ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ታትሞ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገባ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዲሬክተር ሰላማዊት ዳዊት አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሯ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የፓስፖርት አገልግሎት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ሁሉም ዜጎች እስከ ቀጣዩ ታኅሣሥ ወር ድረስ አገልግሎቱን ያገኛሉ፤ ብለዋል፡፡

በሙስና እና በብልሹ አሠራር የተጠረጠሩ 53 የተቋሙ ሠራተኞች እና ደላሎች፣ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው እየታየ እንደኾነም፣ ዲሬክተሯ ተናግረዋል፡፡