ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከክሶቻቸው በአንዱ ላይ ተፈረደባቸው

Your browser doesn’t support HTML5

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፣ በቀድሞ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እና ኢነጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዲሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ፣ የቅጣት ብይን አሳለፈ፡፡

ከራዳር እቃዎች የግዥ ሒደት ጋራ የተያያዘውን ክስ ሲያይ የቆየው ፍ/ቤት፣ ትላንት ኀሙስ ባዋለው ችሎት፣ በተከሳሹ ላይ የሦስት ዓመት ከሰባት ወር እስራት ቅጣት መበየኑን ጠበቃቸው አቶ ሃፍቶም ከሰተ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

አቶ ሃፍቶም፣ ስለ ቅጣት ውሳኔው እንዳብራሩት፣ የሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው አጠቃላይ የፍርድ ሒደት መዘግየት ይታይበታል፤ ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።