የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት፣ በመላው ዓለም ገበሬዎች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ የሚከታተሉት የአሜሪካ ገበሬዎች፣ በእነርሱም ላይ ያለውንም አንድምታ ያጤናሉ።
በዲኬተር-ኢሊኖይ ግዛት የሚገኘው የአዳም ብራውን እርሻ፣ ከዩክሬን የጦር ግንባር በ8ሺሕ700 ኪሎ ሜትር ይርቃል።
ኾኖም፣ ከባድ መሣሪያ እና ሚሳዬል በዚያኛው የዓለም ክፍል ሲተኮስ፣ በመካከለኛው አሜሪካ የሚገኘው አዳም ብራውን፥ የበቆሎው ማሳ ላይ ያረፈ ያህል ይሰማዋል።
ሌሎች ሀገራት፣ ከዩክሬን የሚያስገቡትን ምርት በመተካታቸው፣ በዚኽ ዓመት፣ የስንዴ ዋጋ፣ በሩሲያ ወረራ የመጀመሪያ ወር ላይ ተመዝግቦ ከነበረው ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ዋጋ ወርዶ፣ 50 በመቶ ቀንሷል። የበቆሎ ዋጋም፣ ባለፈው ሚያዝያ ወር ለዐሥር ዓመት ካሳየው ከፍተኛ ዋጋው ቀንሷል። ሩሲያ፣ በዩክሬን የውጭ ገበያ አቅርቦት መሠረተ ልማት ላይ በምታደርሰው ጥቃት ምክንያት፣ የዓለም ገበያ ተናግቷል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ፡፡