ስለ አዕምሮ ጤና የግልጽ ንግግር ባህልን ለማጠናከር ያለመ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች መድረክ ተካሔደ

Your browser doesn’t support HTML5

ስለ አዕምሮ ጤና የግልጽ ንግግር ባህልን ለማጠናከር ያለመ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች መድረክ ተካሔደ

በዩናይትድ ስቴትስ፣ በአብዛኛው በሥነ መድኃኒት እና የመድኃኒት ተኮር የምርምር ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ወጣት እና አንጋፋ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ተገናኝተው፣ ስለ አዕምሮ ጤና የግልጽ ንግግር ባህልን ስለማጠናከር ተወያይተዋል።

የበርካታ ወጣቶች ሕይወት ተጋላጭ ከኾነባቸው የጤና ችግሮች መካከል አንዱ የአዕምሮ ሕመም ነው። ሕመሙን አስመልክቶ፥ በቂ ግንዛቤ፣ ውይይት እና ደጋፊ አገልግሎት አለመስፋፋቱ፣ የባለብሩህ ተስፋ ወጣቶች ሕይወት በአጭሩ እንዲቀጭ ስለማድረጉም ይሰማል።

ኹኔታውን ለመቀየር፣ ሞያዊ ርብርብ በማድረግ ላይ ከሚገኙ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ተቋማት መካከል አንዱ የኾነው ኢፓድ፣ ከሰሞኑ የዕውቀት እና ልምድ ልውውጥ መድረክ አሰናድቷል።

በዚኽ ጉዳይ ላይ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።