በኢትዮጵያ የወባ ሟቾች ብዛት 27 በመቶ እንደጨመረ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ በወባ በሽታ የተነሣ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ27 በመቶ እንደጨመረ ያስታወቁት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ ከ3ነጥብ3 ሚሊዮን በላይ ሕሙማን መኖራቸውን ገልጸዋል።

ከሕሙማኑ የሚበዙት በኦሮሚያ ክልል እንደሚገኙ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበርያ ቢሮ /UN-OCHA/ ባለፈው ሳምንት ያወጣው ሪፖርት ሲጠቁም፣ በዐማራ እና በሲዳማ ክልሎችም የወባ በሽታ ስርጭት እንደጨመረ አመልክቷል።