አንድ ወር የሞላው የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት አሁንም ቀጥሏል
Your browser doesn’t support HTML5
በእስራኤል እና በሐማስ መካከል አንድ ወር ያስቆጠረው ጦርነት በጋዛ ምድር ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በንፁሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት በከፍተኛ ኹኔታ እየጨመረ በመምጣቱም ዩናይትድ ስቴትስ እና ዓለም አቀፍ መሪዎች ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ጊዜያዊ የተኩስ ማቆም እንዲደረግ እየጠየቁ ሲሆን፣ እስራኤል በበኩሏ የ240 ታጋቾቿ ሰብዓዊ ቀውስ ቅድሚያ መፈታት እንዳለበት ትገልጻለች።