ዐቃቤ ሕግ ለ23 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች የ96 ምስክሮችን ዝርዝር ለፍርድ ቤት አቀረበ

Your browser doesn’t support HTML5

የዐማራ ክልልን ቀጥሎም የፌዴራሉን ሥልጣን በኃይል ለመቆጣጠር የሽብር ተግባር እንደፈጸሙ ተጠርጥረው፣ ላለፉት ስምንት ወራት ያህል በእስር ላይ የሚገኙት ተከሳሾቹ፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ፣ ትላንት ሰኞ ውድቅ ተደርጓል፡፡

ተከሳሾቹም የክስ መቃወሚያቸውን፣ በጠበቆቻቸው አማካይነት አቅርበዋል፡፡

ከተከሳሾቹ ጠበቆች መሀከል ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝን አስተያየት በማካተት ኬኔዲ አባተ ተጨማሪ ዘገባ ልኳል፡፡