በኔፓል የመሬት መናወጥ 157 ሰዎች ሞቱ

ፎቶ ኤፒ (ኅዳር 4፣ 2023)

በኔፓል ዓርብ ምሽት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 157 መድረሱ ተነግሯል። በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችም ቤት አልባ ሆነዋል።

ከአደጋው የተረፉት፣ የሟቾችን አስከሬን፣ በሂንዱ ባህል መሠረት በእሳት አቃጥለዋል።

መንግስት ትኩረቱ ምግብ ማዳረስ እና እጅግ ቀዝቃዛ በሆነው ምሽት ደጅ ላይ ለሚያድሩት በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ግዜያዊ መጠለያ ማዘጋጀት እንደሆነ አስታውቋል።

ተራራማ በሆነችው ኔፓል የመሬት መንቀጥቀጥ የተለመደ ሲሆን፣ ከስምንት ዓመታት በፊት በደረሰ መናወጥ 9 ሺሕ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።