በኢትዮጵያ በመንግሥት አካላት እንደታወከ የተገለጸው የሲቪክ ምኅዳሩ “ችግር ላይ ነው” ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ከሚታዩት የትጥቅ ግጭቶች ጋራ በተያያዘ እያጋጠሙ ያሉ ልዩ ልዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የአገሪቱን የሲቪክ እና የፖለቲካ ምኅዳር እያጠበቡት እንደሚገኙ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶር. ዳንኤል በቀለ ገለጹ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ 75ኛ ዓመትን ለማክበር፣ ዛሬ በተዘጋጀው ሥነ ሥርዐት ላይ የተሳተፉ የልዩ ልዩ ድርጅቶች ተወካዮችም፣ የብዙኀን መገናኛዎችንና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን እንቅስቃሴዎች የሚያውኩ ተግባራት በመንግሥት አካላት እንደሚፈጽሙ ገልጸው፣ በዚኽም ምክንያት፣ የሲቪክ ምኅዳሩ እየጠበበ መምጣቱ አሳስቦናል፤ ብለዋል፡፡