ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ፎረም መገለሏ “የወደብ ጥያቄዋን አጠናክሮታል”

Your browser doesn’t support HTML5

በቀይ ባሕር አካባቢ ያለው አሁናዊ ተለዋዋጭ ኹኔታ፣ ኢትዮጵያን ለጂኦፖለቲካዊ ተጋላጭነት ስጋት እንደሚዳርግ፣ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የመካከለኛው ምሥራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሙሐመድ ሰዒድ ገለጹ፡፡

እ.አ.አ በ2018 ኢትዮጵያን ከአባልነት በማግለል የተቋቋመው የቀይ ባሕር ፎረም፣ ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚያነሣቸው፣ በአካባቢው የራስን ወደብ የመሻት ፍላጎቶች፣ አንዱ ምክንያት ስለመኾኑም ተመራማሪው ይናገራሉ፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካን በቅርበት የሚከታተሉት ኤርትራዊው አቶ ዮሐንስ ክፍሌ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ፥ በቀይ ባሕር ጉዳይ ላይ ይመለከተኛል ማለቷ ትክክል አይደለም፤ ሲሉ ይሞግታሉ፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡