የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ኢኮኖሚያዊ ጫና ለአፍሪካ ሀገራት ፈተና እንደሚኾን ተጠቆመ

Your browser doesn’t support HTML5

የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት፣ የሸቀጦችን ዋጋ በማናር፣ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጫና እንደፈጠረ የገለጹ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ፣ ግጭቱ ተባብሶ አካባቢያዊ ቅርጽ ከያዘ፣ ለአፍሪካ ሀገራት ፈተና እንደሚኾን ተናገሩ፡፡

ግጭቱ አካባቢያዊ ቅርጽ በመያዙ፣ የወጪ እና ገቢ ምርት መመላለሻ የኾኑት እንደ ሲውዝ ቦይ ያሉት የባሕር ሰርጦች ሊዘጉ እንደሚችሉ የጠቀሱት ባለሞያው፣ ይህ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ቀውስን እንደሚያስከትል ይጠቁማሉ፡፡ በዚኽም፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ፣ የአፍሪካ ሀገራት የበለጠ ተጎጂ ሊኾኑ እንደሚችሉ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡