በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ እንዲቀጥል የተመድ የባለሞያዎች ቡድን ጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው የባለሞያዎች ቡድን፣ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራው እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ በኹሉም ተፋላሚ ኀይሎች፣ ጭካኔ የተሞላባቸው ዘርፈ ብዙ ግፎች እንደተፈጸሙ የገለጸው ቡድኑ፣ እንዲህ ዓይነት የመብቶች ጥሰት ወደፊትም ሊቀጥል እንደሚችል፣ የባለሞያዎች ቡድኑ ሐላፊ ሞሐመድ ቻንዴ ኦትማን አሳስበዋል፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኝ አንድ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኅብረትም፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት በክልሉ ተፈጽመዋል ያላቸው፣ “የጦር ወንጀሎች እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት”፣ ገልለተኛ በኾኑ ዓለም አቀፍ አካላት እንዲጣሩ ጠይቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ቃለ መጠይቅ የሰጡት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ በርኸ፣ በጦርነቱ ወቅትም ይኹን አሁንም ድረስ፣ በክልሉ እየተፈጸሙ ላሉት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ፍትሕ እና ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል፤ ብለዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡