በእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ባይደን ጥንቃቄ የተመላበት ርምጃ ይጠበቅባቸዋል

Your browser doesn’t support HTML5

እስራኤል፣ በጋዛ ላይ ለማካሔድ ያቀደችው የተቀናጀ የእግረኛ ጦር ዘመቻ፣ እውን ሊኾን በተቃረበበት፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ አጋር ለኾነችው እስራኤል ያላቸውን የማያወላውል ድጋፍ፣ ሚዛናዊ የማድረግ ፈተና ከፊታቸው ተደቅኗል።

ይኸውም፣ ለጋዛውያን ሲቪሎች ኹነኛ ጥበቃ እንዲደረግ፣ እየቀረበ ላለው ዓለም አቀፍ ግፊት ምላሽ መስጠትንና የመካከለኛው ምሥራቅን እንዳያተራምስ የሚያሰጋውን መጠነ ሰፊ ጦርነት ማስቀረትን ይጨምራል።

የአሜሪካ ድምፅ የዋይት ሐውስ ቢሮ ሓላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ያደረሰችን ዘገባ ነው፡፡