የኢትዮጵያዊው የሕፃናት መጽሐፍ ዓለም አቀፍ ሽልማትን አሸነፈ

Your browser doesn’t support HTML5

በየዓመቱ ለማኅበረሰባቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሥነ ጥበብ ባለሞያዎችንና ደራስያንን የሚሸልመው ዓለም አቀፉ ጎርማንድ ሽልማት፣ “ከአርሶ አደሮች አገር የተላከ ደብዳቤ” በሚል ርእስ፣ በኢትዮጵያዊው ዶክተር ወርቁ ለገሰ ሙላት የተጻፈውን የሕፃናት መጽሐፍ በአሸናፊነት መርጧል።

ለውድድሩ፣ ከመላው የዓለም ሀገራት የተሰበሰቡ 100ሺሕ መጻሕፍት ተሰብስበዋል፡፡ ከእነዚኽ መካከል በአሸናፊነት የተመረጠው የዶክተር ወርቁ ለገሰ መጽሐፍ፣ በዋናነት በኢትዮጵያ የገጠር ትምህርት ቤቶች ውስጥ በነጻ ይሰራጫል፡፡ ይኸውም፣ ሕፃናት ስለ አገራቸው ታሪክ እንዲማሩና የማንበብ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ እንደሚያግዝ፣ ደራሲው እና በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱትን ሥዕሎች የሣለው ዳንኤል ጌታሁን፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡