የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለቁልፍ የጸጥታ ጉዳዮች ውይይት ዋሽንግተን ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንተኒ አልባኔዝ፣ የአራት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ፣ ዛሬ ሰኞ፣ ወደ ዋሽንግተን መጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው፣ አውስትራሊያ፣ ብሪታንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ በመሠረቱትና በቁልፍ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረው ጥምረት በሚያደርገው ውይይት ላይ ይሳተፋሉ፡፡ በዚኽም፣ የኒውክሌር ተሸካሚ ሰርጓጅ መርከቦች ስምምነትን አስመልክቶ፣ አንዳች ኹነኛ እመርታን እንደሚያሳኩ ይጠበቃል፡፡

ፊል መርሰር ከሲድኒ ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።