በመኪና ላይ በተጠምደ ቦምብ በደረሰ ፍንዳታ የሶማሊያ የፀጥታ አባላት ተገደሉ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል (ኤፒ)

ፎቶ ፋይል (ኤፒ)

ከሶማሊያ መዲና ዳርቻ በሚገኝ አንድ ወታደራዊ ካምፕ ላይ፣ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ባደረሰው ፍንዳታ፣ 6 የፀጥታ አባላት ሲገደሉ፣ ሰባት ሌሎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ አንድ የፀጥታ ባለሥልጣን እና የአካባቢ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ዛሬ ማለዳ ለደረሰው ጥቃት አል ሻባብ ወዲያውኑ ኃላፊነት ወስዷል።

አጥፍቶ ጠፊው በርካታ ቦምብ የተጠመደበትን መኪና፣ ከሞቃዲሹ 20 ኪ ሜ ላይ ወደሚገኝ የሶማሊያ ወታደራዊ ፖሊስ ካምፕ ነድቶ ሲገባ ፍንዳታው መድረሱ ታውቋል።

ወታደሮች እየመጣ ባለው መኪና ላይ ቢተኩሱም፣ መስኮቶቹ በብረት በመሸፈናቸው፣ መኪናው ወደ ካምፑ ዘልቆ ሊገባ ችሏል ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፀጥታ ባለስልጣን ለቪኦኤ ተናግረዋል።

///