የምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች አንዳንድ ወረዳዎች የከፋ ረኀብ ተጋርጦባቸዋል

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች አንዳንድ ወረዳዎች፣ ረኀብ እንደተጋረጠባቸው፣ ነዋሪዎች ገለጹ።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የወረዳዎቹ ነዋሪዎች፣ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ለዓመታት በዘለቀው ግጭት የተነሳ ለከፋ ረኀብ እንደተጋለጡ ተናግረዋል።

ከፍተኛ የሰብአዊ ርዳታ እጦት እንዳለባቸው ነዋሪዎቹ ጠቅሰው፣ አሁንም በርካታ የወረዳዎቹ ሕፃናት፣ በረኀብ እየተሠቃዩ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

በጉዳዩ ላይ፣ ከምዕራብ ወለጋ እና ከቄለም ወለጋ ዞኖች የጤና ተቋማት እና ቡሳ ጎኖፋ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ እና ቡሳ ጎኖፋ፣ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡