በጉራጌ እና በቀቤና ብሔረሰቦች ግጭት ከመቶ በላይ ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ፣ በጉራጌ እና በቀቤና ብሔረሰቦች አባላት መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ 123 ሰዎች እንደተያዙ፣ የዞኑ አስተዳዳር አስታወቀ።

የአስተዳደሩ ሓላፊ አቶ ኤልያስ ሽበርጋ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ በግጭቱ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባልን ጨምሮ አራት ሰዎች እንደተገደሉ አረጋግጠው፣ ከአንድ መቶ በላይ የከተማው ነዋሪዎች ደግሞ እንደቆሰሉ ተናግረዋል።

አሁን ላይ የወልቂጤ ከተማ፣ መረጋጋት እንደሚታይበትና ወደ መደበኛ እንቅስቃሴውም እንደተመለሰ አቶ ኤልያስ ሽበርጋ ገልጸው፣ ከውድመት የተረፉ የመንግሥት ቢሮዎች እና የግለሰብ ሀብቶች በመጣራት ላይ ናቸው፤ ብለዋል።

የወልቂጤ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ ከተማው እየተረጋጋ ቢኾንም፣ ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡