በወልቂጤ ከቀቤና ልዩ ወረዳ አደረጃጀት ጋራ በተያያዘ ግጭት ጉዳት መድረሱ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ፣ በጉራጌ እና በቀቤና ብሔረሰብ ተወላጆች መካከል ተፈጠረ በተባለ በጦር መሣሪያ የታገዘ ግጭት፣ ቢያንስ አንድን የፖሊስ አባል ጨምሮ አራት ሰዎች እንደተገደሉ፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

የግጭቱ ዋና መንሥኤ፥ የቀቤና ከተማ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጥቶ በልዩ ወረዳ እንዲደራጅ ዐዲስ በተዋቀረው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት፣ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ከመወሰኑ ጋራ ተያይዞ፣ ቀደም ሲል በወሰን ጉዳይ የተፈጠረው አለመግባባት በመካረሩ እንደኾነ፣ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል።

በግጭቱ ሰዎች እንደተጎዱና ንብረትም እንደወደመ ያመለከተው የጉራጌ ዞን የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ ዕዝ፣ የሰዓት እላፊ ገደብ እንደተጣለ፣ የዞኑ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ መምሪያ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።