በባሕር ዳር ሰባታሚት አካባቢ ግጭት የጥበበ ግዮን ልዩ ሆስፒታል አገልግሎት እንዳቆመ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

ከባሕር ዳር ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሥር የሚገኘው የጥበበ ግዮን ልዩ ሆስፒታል፣ መደበኛ አገልግሎት መስጠት እንዳቆመ፣ የሆስፒታሉ ሐኪሞች እና ሠራተኞች ገለጹ።

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡና ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የጤና ባለሞያዎች ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት ያቋረጠው፣ በቅርቡ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በፋኖ ቡድን ታጣቂዎች መካከል፣ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ፣ በአቅራቢያው የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ነው፡፡ በግጭቱ ለደኅንነታቸው የሰጉ የሕክምና ባለሞያዎች፣ ሆስፒታሉን እየለቀቁ ወጥተዋል፤ ብለዋል የጤና ባለሞያዎቹ፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁለት የዩኒቨርሲቲው ባለሥልጣናት፣ የሆስፒታሉ ሠራተኞች፣ ከትላንት እሑድ ጀምሮ፣ በከፊል በሥራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ ተናግረዋል፡፡