በትግራይ ክልል ሕይወታቸው ላለፈ የቀድሞ ተዋጊዎች የሦስት ቀናት ኀዘን ታወጀ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሕይወታቸው ያለፈ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ለመዘከር፣ የሦስት ቀናት ኀዘን ታውጇል።

ከነገ ቅዳሜ፣ ጥቅምት 3 እስከ 5 ድረስ በታወጀው የኀዘን ቀን፣ በጦርነቱ ሕይወታቸው ያለፉ ተዋጊዎች፣ ክብራቸውን በሚመጥን ሥነ ሥርዐት እንደሚዘከሩ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አስታውቀዋል። ለሟች ቤተሰቦችም፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የዕዝን ድጋፍ ለመስጠት እንደተዘጋጀ፣ ፕሬዚዳንቱ አክለው ገልጸዋል።

ኀዘኑን ለመካፈል ወደተለያዩ አካባቢዎች በርከት ብለው የሚሔዱ፣ የኀዘንተኛ ቤተሰቦች ዘመዶችንና ቀራቢዎችን፣ በመቐለ ከተማ መመልከቱን ገልጾ ዘገባ ያደረሰን፣ ሙሉጌታ አጽብሓ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።