የቅሬታ አጣሪ ቴክኒክ ኮሚቴው ከዳግም ቅሬታ እንዳላዳናቸው ሠራተኞች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የቀድሞ የደቡብ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች የድልድል ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ሠራተኞችን ቅሬታ እንደተመለከተ ገልጾ፣ ውጤቱን ትላንት ማክሰኞ ይፋ አድርጓል።

ቅሬታ አቅራቢ ሠራተኞች በበኩላቸው፣ በአጣሪ ኮሚቴው ጉዳያቸው ከታየላቸው 2000 ሠራተኞች ውስጥ፣ የድልድል ማስተካከያ ያገኙት 120ዎቹ ብቻ እንደኾኑ ጠቅሰው፣ የብዙኀኑ ባለጉዳይ ቅሬታ አሁንም ተገቢ ምላሽ እንዳላገኘ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አመልክተዋል።

ከፌዴራል መንግሥት የተወከሉት የሠራተኞች ምደባ ቴክኒክ ኮሚቴ አባል አቶ ፈለቀ መኰንን፣ ሠራተኞቹ ባቀረቡት መረጃ መሠረት ተደልድለዋል፤ ሲሉ አስታውቀዋል።

ለኹሉም ቅሬታ አቅራቢዎች ምላሽ እንዳልተሰጠ ያልሸሸጉት አቶ ፈለቀ፣ ተጨባጭ እና ተቀባይነት ያለው ቅሬታ አቅርበዋል፤ ላሏቸው ሠራተኞች፣ የድልድል ማስተካከያ እንደተደረገ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።