ጉዳት ለደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል ተለዋዋጭነት ባለው የጸጥታ ኹኔታ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች ተመልሰው ሥራ እንዲጀምሩ፣ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ፣ የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾች እና ላኪዎች ማኅበር ጠየቀ፡፡

የማኅበሩ ዋና ዲሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ በክልሉ በተስፋፋው ግጭት፣ አምስት የአበባ እርሻዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ወደ ሦስት ሺሕ የሚደርሱ ሠራተኞቻቸውም ተበትነዋል፡፡ የተጎዱትን እርሻዎች መልሶ ሥራ ለማስጀመር፣ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግና የደኅንነት ዋስትናም እንዲሰጥ፣ ዲሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

ማኅበሩ ይህንኑ ጥያቄውን፥ ለግብርና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና ለዐማራ ክልል መንግሥት ማቅረቡን፣ አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጠው የግብርና ሚኒስቴር፣ በአበባ እርሻዎቹ ላይ የደረሰው ጉዳት በሚኒስቴሩ በተቋቋመ ግብረ ኀይል እንደተጠና ጠቅሶ፣ በቅርቡ ምላሽ እንደሚሰጣቸው አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።