በሐማስ ድንገተኛ ጥቃት የተለያዩ ሀገራት ዜጎች እንደተገደሉ የእስራኤል ኤምባሲ ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የጋዛው ታጣቂ ቡድን ሐማስ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ማለዳ፣ በእስራኤል ላይ በምድር፣ በአየር እና በባሕር በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ከተገደሉት ከ700 በላይ ሰዎች መካከል፣ የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎች እንደሚገኙባቸው፣ ዐዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ኢትዮጵውያን ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመው፣ ይህን ለማረጋገጥ የማጣራት ሥራ እንደሚሠራ አመልክተዋል፡፡

በዐዲስ አበባ የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ኤምባሲዎች፣ አቋማቸውን እየገለጹ እንደኾነ የተናገሩት አምባሳደር አለልኝ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን፣ እስከ አሁን ድረስ በይፋ የተሰማ ነገር እንደሌለ ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።