ለሆራ ፊንፊኔ በዓል አከባበር በርካቶች በጠንካራ የጸጥታ አጠባበቅ ውስጥ ወደ ዐዲስ አበባ እየጎረፉ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

በዐዲስ አበባ ከተማ፣ ነገ ቅዳሜ፣ የሚከበረውን የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ለመታደም፣ በርካቶች ወደ ከተማዋ በመግባት ላይ ናቸው።

የከተማዋ አስተዳደር፣ ለክብረ በዓል እንግዶቹ ተገቢ አቀባበል ለማድረግ እንደተዘጋጀ ሲገልጽ፣ ከንቲባ አንዳነች አበቤም፣ የጸጥታ ኃይሎች የከተማዋን ሰላም እና ጸጥታ እየተከታተሉ እንደኾነ፣ ዛሬ ከቀትር በፊት፣ በሸራተን ሆቴል በተካሔደው አምስተኛው የኢሬቻ ፎረም ላይ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮም፣ በጸጥታው ረገድ በበቂ እንደተዘጋጀ ገልጾ፣ በዓሉ በዩኔስኮ በቅርስነት እንዲመዘገብ የጥናት ሥራዎች እየተካሔዱ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ከነገው የሆራ ፊንፊኔ በዓል አከባበር ጋራ በተያያዘ፣ በተለይ ወደ ዐዲስ አበባ በሚያመሩ ተጓዦች ላይ ፍተሻዎች እንደተጠናከሩ መንገደኞች ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።

ከምሥራቃዊው የዐማራ ክልል ወደ ዐዲስ አበባ የሚያቀኑ መንገደኞች፣ ሸኖ ከተማ ላይ፣ በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ወደ አገሪቱ ርእሰ መዲና ከመግባት እንደተከለከሉ፣ ያቀረቡትን ቅሬታ ጠቅሰን ትላንት መዘገባችን ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።