በመስቃን ወረዳ የሚኖሩ እናትና ልጅ በታጣቂዎች ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመስቃን ወረዳ በሚኖሩ የማረቆ ብሔረሰብ ተወላጅ በኾኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በተፈጸመ ጥቃት፣ እናት እና ልጅ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ ስድስት ሰዎች ክፉኛ ቆስለው ወደ አዳማ ጠቅላላ ሆስፒታል እንደተወሰዱ፣ ጎረቤቶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ተናግረዋል።

የምሥራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ባለሥልጣናት እና የመስቃን ወረዳ አመራሮች፣ ስልኮቻቸውን ስለማያነሡና ቢያነሡም ፈቃደኛ ባለመኾናቸው፣ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ምላሽ እና አስተያየት ለማካተት አልቻልንም።

የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ንጉሤ መከ፣ ተስብስበው ቡና ሲጠጡ የነበሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ፣ በታጠቀ ቡድን በተፈጸመ እኩይ ጥቃት ሁለት ሲቪሎች እንደተገደሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።

በአካባቢው፣ ካለፈው መስከረም 16 እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በዘለቀ ግጭት፣ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ፣ ከትላንት በስቲያ፣ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወቃል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።