ዋይት ሐውስ ለዩክሬን ድጋፉ እንዲቀጥል ጥረት እያደረገ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

የምዕራቡ ዓለም ለዩክሬን በሚያደርገው ድጋፍ ስንጥቃት እየታየበት ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት፣ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት መሀከል በጉዳዩ ላይ መከፋፈል አለ፡፡ ከኔቶ የጦር ቃል ኪዳን አባል ሀገራት ውስጥ ደግሞ፣ ዐዲሱ የስሎቫኪያ ፕሬዚዳንት፣ አገራቸው ለዩክሬን የምትሰጠውን ድጋፍ ቀጣይነትን አስመልክቶ ጥርጣሬ ገብቷቸዋል፡፡
ዋይት ሐውስ ግን፣ ለዩክሬን በሚሰጠው ድጋፍ ቀጣይነት ቁርጠኛ እንደኾነ፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንቱ፣ የኮንግረስ ሪፐብሊካን አባላት፣ 24 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ ለዩክሬን እንዲሰጥ ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ እየተማፀኑ ነው።
አኒታ ፓወል ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።