ሰባት የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች ሁለተኛ ዙር ክርክራቸውን አደረጉ

Your browser doesn’t support HTML5

የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ተፎካካሪዎች፣ ትላንት ምሽት ሁለተኛ ዙር ክርክራቸውን ለሁለት ሰዓታት አድርገዋል። የመጀመሪያውን ቅድመ ምርጫ፣ ከአራት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማድረግ በታቀደበት ኹኔታ፣ በክርክሩ ከተሳተፉት ዕጩዎች በበለጠ፣ ለመሳተፍ ያልፈቀዱት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ የበለጠ ተቀባይነት እንዳላቸው የሕዝብ አስተያየት ውጤቶች ያሳያሉ።

ይህም ኾኖ ተፎካካሪዎቹ፣ የድምፅ ሰጪዎችን ትኩረት ለማግኘት ተስፋ ያደርጋሉ። የቪኦኤ የዋሽንግተን ከፍተኛ ዘጋቢ ካሮሊን ፕረሱቲ የላከችውን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ)