እያየለ ባለው የአል-ሻባብ ጥቃት ላይ የሶማሊያ ጎረቤቶች ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

አል-ሻባብ፣ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ እና በሶማሊያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ የሚያደርሰው ጥቃት እየጨመረ መሔድ፣ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት እንደሚኾን፣ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ተናግረዋል።

የጥቃቱ መጨመር፣ እ.አ.አ. ከ2007 ጀምሮ፣ ከሶማሊያ መንግሥት ጋራ ሲሠራ የቆየው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ልዑክ፣ ቀስ በቀስ አገሪቱን ከመልቀቁ ጋራ ሲያያዝ ደግሞ፣ ስጋቱን እንደሚያጠናክረው አመልክተዋል፡፡

የሶማሊያ አጎራባች ሀገራት ደኅንነታቸውን ለማስጠበቅ፣ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ትብብራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም፣ ምሁራኑ አሳስበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።