በጋምቤላ ከ61 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች በጎርፍ እንደተፈናቀሉና እንደተጎዱ ክልሉ ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በጋምቤላ ክልል የተከሠተው ጎርፍ፣ ከ25ሺሕ በላይ ሰዎችን ከቀዬአቸው ሲያፈናቅል፣ ከ36ሺሕ በሚልቁት ላይ ደግሞ ጉዳት ማድረሱን፣ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

ጎርፉ አሁንም፣ በተጨማሪ ሰዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ፣ ክልሉ ገልጿል፡፡የጋምቤላ ከተማ ጤና ጽሕፈት ቤት ሓላፊ እና የከንቲባው ተወካይ አቶ ሳይመን ቲያቺ፣ በአደጋው ተፈናቅለው በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተጠለሉ ሰዎችን ወደ ሌላ ጊዜያዊ መቆያ ለመውሰድ እንደታቀደ አመልክተዋል።

የጋምቤላ ክልል ጸጥታ እና ሰላም ግንባታ ቢሮ ምክትል ሓላፊ እና የክልሉ ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ዑሞድ ዑሞድ በበኩላቸው፣ ባሮን ጨምሮ የክልሉ ወንዞች፣ በዝናም ሳቢያ እየሞሉ የሚያደርሱትን ከፍተኛ ጉዳት ለመቀነስ፣ አስተዳደሩ ከፌዴራል መንግሥት ጋራ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ግን፣ “ጥናት ያስፈልጋል” ሲሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።