በምዕራብ ጎንደር ኩመር መጠለያ ጣቢያ ዘጠኝ ሱዳናውያን ስደተኞች በኮሌራ ወረርሽኝ እንደሞቱ ተነገረ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ውስጥ በተቋቋመ የኩመር መጠለያ ጣቢያ፣ የኮሌራ ወረርሽኝ እንደተከሠተና ዘጠኝ ሱዳናውያን ስደተኞች እንደሞቱ፣ 395 ሰዎች ደግሞ እንደታመሙ፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር/UNHCR/ አስታወቀ፡፡

የተቋሙ የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ማርጋሬት አትዬኖ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በሱዳኑ ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ብዛት፣ ከ35ሺሕ በላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ከእኒኽም ውስጥ፣ 10ሺሕ የሚደርሱቱ፣ በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ በሚገኝ የኩመር መጠለያ ጣቢያ እንደተጠለሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሸርቆሌ መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ፣ በየቀኑ 50 ሰዎች፣ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የጠቀሱት ሐላፊዋ፣ የዓለም ምግብ ድርጅት እና የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት፣ ለኢትዮጵያ ሲሰጡት የነበረውን ርዳታ በማቋረጣቸው፣ በስደተኞች አገልግሎት ላይ ጫና እንደፈጠረም አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።