የዐማራ ክልል ግጭት በመማር ማስተማር ዝግጅት ላይ ጫና ማሳደሩ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል የተስፋፋው ግጭት እና አለመረጋጋት፣ በክልሉ የመማር ማስተማር ሒደት ላይ ጫና ማሳደሩን፣ ወላጆች እና መምህራን ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ፡፡

በክልሉ፣ የግጭት ኹኔታ እና የአለመረጋጋት ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች፣ የተማሪዎች ምዝገባ ገና እንዳልተጀመረ አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ይኸው፣ ተለዋዋጭ የጸጥታ ይዞታ፣ በውይይት ዘላቂ እልባት ካላገኘ በቀር ሰላሙ አስተማማኝነት እንደማይኖረውና በስጋት ውስጥ እንደሚያቆያቸው አመልክተዋል፡፡

የትጥቅ ግጭቱ፣ በ2016 ዓ.ም. የመማር ማስተማር ሒደት ላይ ያሳደረውን ጫና አስመልክቶ፣ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ይኹን እንጂ፣ በክልሉ፣ ዕድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ሕፃናት ውስጥ እስከ አሁን የተመዘገቡት 37 በመቶ ብቻ እንደኾኑ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ከክልሉ ወቅታዊ ኹኔታ አንጻር፣ የመማር ማስተማር ዝግጅቱ ስለሚገኝበት ደረጃ፣ ክትትል ማድረግ እንዳልቻለ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።