በጎሮ ዶላ ወረዳ በዐዲሱ የዞን መዋቅር ተቃውሞ የተማሪ ምዝገባ እንዳልተካሔደ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል ዐዲስ በተዋቀረው የምሥራቅ ቦረና ዞን፣ የጎሮ ዶላ ወረዳ አላግባብ ተካላለች፤ በሚል የተነሣውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የዘንድሮ የተማሪዎች ምዝገባ እስከ አሁን እንዳልተከናወነ ተገልጿል።

ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ አጎራባች ወረዳዎች እየወሰዱ ለማስመዝገብ ቢሞክሩም፣ ትምህርት ቤቶች እና የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ በመኾናቸው እንደተቸገሩ ተናግረዋል፡፡

የጎሮ ዶላ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤትም፣ ካለፈው ዓመት ነሐሴ 23 ቀን ጀምሮ ሊደረግ የነበረው የተማሪዎች ምዝገባ፣ እስከ አሁን አለመከናወኑን አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።