በኢትዮጵያ በተስፋፋው ግጭት የስብሰባ ቱሪዝም እየቀነሰና የሆቴል ዘርፉም እየተጎዳ እንደኾነ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ባለው የትጥቅ ግጭት እና አለመረጋጋት ምክንያት፣ የስብሰባ ቱሪዝም እየቀነሰ መምጣቱን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ማኅበራት አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ የሆቴል እና ቱሪዝም አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶር. ፍትሕ ወልደ ሰንበት፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ በአለመረጋጋቱ ምክንያት፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን ከዐዲስ አበባ ወደ ሌሎች ሀገራት ማዞር እንደተጀመረ ተናግረዋል፡፡

አጠቃላይ የውጭ ጎብኚዎች ፍሰት እየቀነሰ እንደኾነ የሚገልጹት፣ የዐዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ወሮ. አስቴር ሰሎሞንም፣ የሆቴል ዘርፉም እየተጎዳ እንደኾነና ይነቃቃ ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት በውይይት ሰላም እንዲፈጥሩ ጠይቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።