በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በዐማራ ክልል 764 ሰዎች እንደታሰሩ መርማሪ ቦርዱ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል በተስፋፋው ግጭት ምክንያት ከወጣው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋራ በተያያዘ፣ በተለያዩ አምስት ስፍራዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ዜጎች ቁጥር 764 እንደኾነ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መርማሪ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ብዛቱ ወደፊት በተለያዩ ምክንያቶች ሊቀነስ ወይም ሊጨምር እንደሚችልም፣ መርማሪ ቦርዱ አመልክቷል፡፡

የታሳሪዎቹን ቁጥር በአሁኑ ወቅት በትክክል ማወቅ እንዳልቻለ የገለጸው ደግሞ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።