በተቀዛቀዘው የሐዋሳ የበዓል ግብይት የነጋዴዎች አስተያየት እና የሸማቾች ምላሽ

Your browser doesn’t support HTML5

የዐዲስ ዓመት የበዓል ገበያ፣ በአንዳንድ አቅርቦቶች የዋጋ ጭማሪ ቢያሳይም፣ የተረጋጋ እና ቀዝቀዝ ያለ ነው፤ ሲሉ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ገበያው መቀዛቀዝ ያሳየው፣ በሸማቹ ኅብረተሰብ ዘንድ የገንዘብ እጥረት በመኖሩ ሳይኾን እንዳልቀረ፣ ነጋዴዎች አስተያየታቸውን ተናግረዋል።

ሸማቾች በበኩላቸው፣ በርእሰ ዐውደ ዓመት ሞቅ ደመቅ የሚለው ገበያ፣ ዘንድሮ መቀዛቀዝ የሚታይበት፣ የኑሮ ውድነትን ባስከተለው የዋጋ ጭምሪ እንደኾነ በመጠቅስ ይከራከራሉ።

ዛሬ፣ የበዓል ገበያ የዋለባቸውን ቦታዎች ተዘዋውሮ የቃኘው፣ የሐዋሳው የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ እንደ ወትሮው የደሩ የበዓል ግብይቶችን እንዳልተመለከተ መታዘቡን ገልጾ የሚከተለውን ዘገባ ልኳል።