የዓመቱ ግጭቶች እንዳይባባሱ ሀገር አቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች ጥሪ ቀረበ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ እየተስፋፉ ለሚገኙ ግጭቶች፣ ዘላቂ መፍትሔ የሚቀየስበት ሀገር አቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች፣ 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ፡፡ ድርጅቶቹ፣ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በልዩ ልዩ የአገሪቱ አካባቢዎች፣ በዚኽ ዓመት የታዩት ዐዲስ እና ነባር ግጭቶች፣ በመጪው ዓመትም ተባብሰው እንዳይቀጥሉ፣ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዓመቱ ውስጥ በተፈጠሩ ፖለቲካዊ ግጭቶች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች፣ ከ5ሺሕ900 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ፣ የድርጅቶቹ መግለጫ አመልክቷል፡፡

እየተገባደደ ያለው ዓመት በአንጻሩም፣ የሰላም ተስፋዎች እና በጎ ጅምሮች የታዩበት እንደነበረም ድርጅቶቹ አመልክተዋል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)