የአፍሪካ ሃገራትን የንግድ ትስስር ያጠናክራል የተባለው የነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ የንግድ ልዉውጥ ለመጀመር የሚያስችሏት የንግድ እቃዎች የውል ሰንጠረዥ እና የአገልግሎት ግዴታ ሰነዶች ዝግጅት ማጠናቀቋን በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር የአለም አቀፍ እና ቀጠናዊ ንግድ ትስስር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታገሰ ሙሉጌታ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

በሃገራቱ መካከል ያለዉ ዝግጅት እንደሚለያይ የጠቆሙት የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤቶች ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዉ አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው በትግበራዉ ወቅት የሚኖረው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትም ቢሆን የተለያየ መሆኑ እንደማይቀር ይገልጻሉ፡፡

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት በአባል ሃገራቱ ከተፈረመ አምስት ዓመታት አልፈዉታል። አብዛኞቹ ሃገራት ገና በዝግጅት ምዕራፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን ይህንን የቅድመ ዝግጀት ስራዉ ያጠናቀቁ ስምንት ሃገራት ደግሞ የሙከራ ትግበራ ላይ ይገኛሉ፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ)