የትግራይ ክልል የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮቻቸው እንደታሰሩባቸው ገለጹ
Your browser doesn’t support HTML5
መቀሌ ላይ ለከነገ በስቲያ ለጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአመራር አባሎቻቸው እንደታሰሩባቸው ሦስት የትግራይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ።
ሰልፉን የጠሩት ሣልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ እና ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ናቸው።
ተያዙ ስለተባሉት ሰዎች የከተማዪቱን ፖሊስና የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ቪኦኤ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።