በእስራኤል እርስ በርስ የተጋጩ ኤርትራውያን ከሀገር መባረር እንደሚጠብቃቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በእስራኤል እርስ በርስ የተጋጩ ኤርትራውያን ከሀገር መባረር እንደሚጠብቃቸው ተገለጸ

በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከል፣ በሳምንቱ መጨረሻ፣ በቴል አቪቭ - እስራኤል በተፈጠረ ግጭት፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መጎዳታቸውንና ንብረትም መውደሙን ተከትሎ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት፣ በግጭቱ የተሳተፉ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከሀገር እንደሚያስወጧቸው እየዛቱ ናቸው።

የኤርትራን 30ኛ የነፃነት ቀን አስመልክቶ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ፣ በቴል አቪቭ ተዘጋጅቶ በነበረ ክብረ በዓል ላይ፣ የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች በአንድ ወገንና ተቃዋሚዎች በሌላ ወገን ተሰልፈው በተፈጠረ ኀይል የተቀላቀለበት ግጭት ዐያሌዎች ተጎድተዋል። የፖሊስ አባላትም ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በበኩላቸው፣ የኤርትራን ስም ለማጠልሸት ይሻሉ ያሏቸው ኀይሎች፣ በሁከት እና ንብረት በማውደም ሕጋዊውን ክብረ በዓል ለማስተጓጎል ሞክረዋል፤ ብለዋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።