እንደራሴዎቹ ከመረጣቸው ሕዝብ ጋራ እንዳይወያዩ መከልከላቸውን ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

እንደራሴዎቹ ከመረጣቸው ሕዝብ ጋራ እንዳይወያዩ መከልከላቸውን ገለጹ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአማሮ ኮሬ ዞን እንደራሴዎች፣ ከመረጣቸው ሕዝብ ጋራ ውይይት እንዳያደርጉ መከልከላቸውን ገለጹ።

የዞኑ አስተዳዳሪ በበኩላቸው፣ በዞኑ የጸጥታ ችግር እንዳለና ለሕዝብ ተወካዮቹም ደኅንነት ሲባል፣ ችግሩ እስኪፈታ ድረስ እንዲታገሡ አሳወቅናቸው እንጂ እንዳይወያዩ አልከለከልናቸውም፤ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በጉዳዩ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር አንዱዓለም ነጋ፤ የሕዝብ እንደራሴዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ የመረጣቸውን ሕዝብ የማወያየት መብት እንዳላቸው ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።