ዓሊ ቦንጎን ከሥልጣን ያስወገዱት ወታደራዊ መሪ የሽግግር ፕሬዚዳንት ኾኑ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ዓሊ ቦንጎን ከሥልጣን ያስወገዱት ወታደራዊ መሪ የሽግግር ፕሬዚዳንት ኾኑ

የማዕከላዊቷ አፍሪካ ጋቦን የረጅም ዓመት ፕሬዚዳንት የነበሩትን ዓሊ ቦንጎን፣ ከሥልጣን ያስወገዱት ወታደራዊ መሪ፣ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚዳንት ኾነው ዛሬ ቃለ መሐላ ፈጸሙ፡፡

ጄነራል ብራይስ ኦሊጉዊ ኢንጉዌማ፣ ባለፈው ሳምንት የገለበጧቸው የዓሊ ቦንጎ ቤተሰብ፣ ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ የአገሪቱን የመሪነት ሥልጣን ጨብጦ ኖሯል፡፡

ይኹንና፣ በጋቦን የተካሔደው የመንግሥት ሽረት፣ በእንግሊዘኛ ምኅጻሩ “ሴማክ” ተብሎ በሚጠራው የማዕከላዊ አፍሪካ አካባቢ ሀገራት ማኅበረሰብ፣ ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ የቆዩ መሪዎችን አስመልክቶ ክርክር አሥነስቷል፡፡

ከካሜሩን ዋና ከተማ ከያውንዴ ሞኪ ኤድዊን ኪንድዜካ ያጠናቀረው ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።