የስኳር ቁስል ልባስ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በዓለም ላይ፣ በስኳር በሽታ በሚመጣ ቁስል ምክንያት፣ በየ30 ሰከንዱ የአንድ ሰው እግር በቀዶ ሕክምና እንደሚቆረጥ ጥናቶች ያሳያሉ።

ይህን አስከፊ ሁኔታ ለመቀየር ታዲያ፣ በካሊፎርኒያ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች፣ ለየት ያለ የቁስል ልባስ ፕላስተር ሠርተዋል።

ልባሱ፣ ቁስሉ በተለያዩ ደረጃዎች ያለበትን ኹኔታ ለጤና ባለሞያዎች መረጃ እንደሚያስተላልፍና ማዳንም እንደሚችል ተነግሯል። የቪኦኤዋ ጂኒያ ዱሉ የላከችው ዘገባ እንደሚከተለው ይቀርባል።