ራስ ገዝ የኾነው የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዐዲስ ቻንስለር ተሾመለት

  • መለስካቸው አምሃ

Your browser doesn’t support HTML5

የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከ48 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቻንስለር ተሾመለት፡፡ በአገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለኾነው ለዚኹ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲ፣ ዐዲስ የሥራ አመራር ቦርድም ተሠይሞለታል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ዐዲስ ቻንስለር ኾነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾሙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ “ትምህርት ለትውልድ” በተሰኘው ንቅናቄ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ብር እንደተሰበሰበ አስታውቀዋል፡፡