ከተጠርጣሪዎቹ የተወሰኑት ፍርድ ቤት እንደቀረቡም በመጥቀስ፣ የእስረኞቹን ቤተሰቦች ቅሬታ አጣጥለዋል።
በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ግጭት የታሰሩ ሰዎች ፍ/ቤት እንዳልቀረቡ ቤተሰቦቻቸው ገለጹ
Your browser doesn’t support HTML5
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሻራ ቀበሌ ከተፈጠረው ግጭት እና ግድያ ጋራ በተያያዘ፣ ተጠረጥረው የታሰሩ ሰዎች፣ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ሳምንት እንዳለፋቸው፣ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ደግፌ ደበላ በበኩላቸው፣ ታሳሪዎቹ በከባድ ወንጀል እንደተጠረጠሩና አብዛኞቹም ምርመራ ላይ እንደኾኑ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡